በአማራ ክልል የ2015 ክልል አቀፍ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ልማት ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የ2015 ክልል አቀፍ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ልማት ስራ በዛሬው ዕለት በማእከላዊ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ ተጀምሯል፡፡
መርሃ ግብሩን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀምበር ያስጀመሩት ሲሆን÷የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርሶአደሮች እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በወረዳው 49 ተፋስሶች ውጤታማ መሆናቸው በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ የሹማራ ቀበሌ አበቄለሽ ተፋሰስን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም÷ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስን ጨምሮ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በምናለ አየነው