Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር ህዝባዊ ትስስር የሚያጠናክር ነው – አቶ ቀጄላ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር የህዝቦችን አንድነት የሚያጸና፣ ህዝባዊ ትስስር የሚያጠናክር በዓል መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ።

ሚኒስትሩ የጥምቀት በዓልን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ፥ የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር የህዝቦችን አንድነት የሚያጸና ፤ ህዝባዊ ትስስር የሚያጠናክር በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉ በርካታ ባህላዊ እሴቶች የሚንጸባረቁበት መሆኑን ገልጸው፤ በጎ እና ለህዝቡ አብሮነት የሚጠቅሙትን መጠበቅና ማልማት ያስፈልጋል ብለዋል።

የጥምቀት በዓል ከፍተኛ ቱሪስቶችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚስብ በመሆኑም ኢትዮጵያ ከዘርፉ በርካታ ገቢዎችን እንድታገኝም ያስችላል ነው ያሉት።

በዓሉ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ መሆኑን ጠቁመው ፥ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሚኒስቴሩ ፥ በዓላት ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩና እንዲለሙ የሚሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

የኢፌዴሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ በበኩላቸው ፥ በህዝብ ውስጥ ያሉ ባህላዊ እሴቶችን አውጥቶ ለማሳየትና ለትውልዱም እንዲተላለፍ ከማደረግ አንጻር የሁሉም ሃላፊነት መሆን አለበትም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.