Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ለተጎዱ የአማራና አፋር ክልል ጤና ተቋማት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አማራ እና አፋር ክልል የጤና ተቋማት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና እና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉን ሪች ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤይድ) ጋር በመተባበር ያደረገው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት በአማራ ክልል በ12 ዞኖች በጤና ተቋማት ላይ በደረሰ ጉዳት ከ10 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከጤና አገልግሎት ውጭ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ተወካይ ዶ/ር ኤልሳቤጥ ሰጠኝ ተናግረዋል ።

በተመሳሳይ በአፋር ክልልም በደረሰው ጉዳት በጤና መሰረተ ልማት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ውድመት መድረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ ተወካይ ሁሴን መሃመድ ገልፀዋል፡፡

በዚህም በሪች ኢትዮጵያ የተደረገው ድጋፍ ለስራቸው ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ተናግረዋል ።

ድጋፉ በሁለቱ ክልሎች ለሚገኙ 80 የጤና ተቋማት የሚከፋፈል መሆኑን የሪች ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ መሰረት አሰፋ ገልፀዋል፡፡

በበረከት ተካልኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.