Fana: At a Speed of Life!

የህዝብን ጥያቄ ፈጥኖ የሚፈታ ተራማጅ አመለካከት ያለው አመራር መፍጠር ይገባል – አቶ ኡመድ ኡጅሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የህዝብን ጥያቄ ፈጥኖ ሊፈታ እና ለውጡን ሊያሻግር የሚችል ተራማጅ አመለካከት ያለው አመራር መፍጠር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጅሉ ገለጹ፡፡

በክልሉ በመልካም አስተዳደር ችግር ምክንያት ከህዝብ ሲቀርቡ በነበሩ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ዙሪያ ከክልል፣ ከዞን፣ ከከተማና ከወረዳ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ እንደተናገሩት ፥ በክልሉ የሚታዩት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል።

በክልሉ ህግ ሲጣስ በቸልተኝነት የሚያልፉ ኪራይ ሰብሰሳቢነት የሚስተዋልባቸው አካላት መኖራቸውን ጠቁመው ፥ ኃላፊዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በአግባቡ መፍታት እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል።

በክልሉ የህዝብን ጥያቄ ፈጥኖ ሊፈታና ለውጡን ሊያሻግር የሚችል ተራማጅ አመለካከት ያለው አመራር መፍጠር እንደሚገባም ነው ያስረዱት።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የካቢኔ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፒተር ሆው ፥ በክልሉ በመልካም አስተዳደር ችግር የከተማና የገጠር መሬት፣ የፍትህ ችግር፣ ግብር እና ቀረጥ፣ የፍጆታ እቃዎች እንደሚገኙበት አንስተዋል።

የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመመለስ የክልሉን እድገት ለማፋጠን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ መናገራቸውንም የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.