የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በፓኪስታን ከኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Tamrat Bishaw

January 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ጀማል በከር ጋር ተወያዩ፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽነር ለሊሴ÷ በኢትዮጵያ በሲሚንቶ፣ በማዳበሪያ እና በብረት አምራች ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ካሳየው ዓለማቀፍ ኩባንያ የአሪፍ ሃቢብ ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚ ሞሃመድ ቃሲፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በኢንቨስትመንት ዘርፉ ስላሉ ዕድሎች፣ አማራጮች፣ ማበረታቻዎች፣ የሕግ እና ፖሊሲ ማሻሻያዎች ላይ ከሚሽነር ለሊሴ ነሜ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት አካባቢው ለባለሀብቱ ምቹ እንዲሆን ሰፊ ሥራ መሠራቱንም ለባለሀብቶቹ ማስረዳታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡