የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በትኩረት ይሠራል – አቶ አሻድሊ ሀሰን
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሠላምና ጸጥታ የተከናወኑ አበረታች ሥራዎችን በማጠናከር ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በትኩረት አንደሚሠራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላምና ጸጥታ የ6 ወራት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ የተካሄደ ሲሆን ÷በግምገማው ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ተፈጥሮ የነበረውን ውስብስብ የጸጥታ ችግር ለማስወገድ በተከፈለው መስዋዕትነት አሁን ትልቅ የሠላም ተሥፋ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በሠላምና ጸጥታ የተከናወኑ አበረታች ሥራዎችን በማጠናከር በክልሉ ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ነው ያነሱት።
በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ተፈናቅለው ወደቀያቸው የተመለሱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከፌዴራል መንግስትና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት ለህዝብ ሠላም ሲባል ቀደም ብሎ የከፈተው የሠላም በር አሁንም ክፍት ነው ያሉት አቶ አሻድሊ፥ ይህንን ዕድል ያልተጠቀሙ አካላት አሁንም መጠቀም እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
የክልሉ ሠላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አቢዮት አልቦሮ ፥ አሁን ከተገኘው ሠላም ባሻገር የጠላትን እኩይ እንቅስቃሴ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ የክልሉን ሠላም በዘላቂነት ማረጋገጥ ከሁሉም እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የጸጥታ አመራሮች መገኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!