Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በጋራ 500 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ  ለመገንባት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ማስዳር ኩባንያ የ500 ሜጋ ዋት ሁለት የሶላር ጣቢያ (የፀሐይ ብርሃን ኃይል) በጋራ ለማልማት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ጋር በቃስር አል ሻቲ ቤት መንግሥት ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በዚህም ወቅት ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኃይል ማመንጨት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ኢትዮጵያ ሰፊ የታዳሽ ኃይል ሀብት አላት ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የካርቦን ልቀትን ዜሮ የማድረግ ዒላማ ታዳሽ ሀብታችንን ለመጠቀም እና አስተማማኝ፣ ንፁህ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኃይል ለኢትዮጵያ እና ለሌሎችም ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ዐቅምና እድል ነውም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.