Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታትከፍተኛ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ ከፍተኛ ተወካይ አምባሳደር ራባብ ፋጢማ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው አቶ ደመቀ ፥ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ አገራት፣ የባህር በር  የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት እና ትናንሽ ደሴቶች የደቡብ ደቡብ ትብብርን በማጠናከር የድህነት ቅነሳ እና የዘላቂ ልማት ግቦቻቸውን ለማሳካት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ገልፀዋል ።

እነዚህ ሀገራት በተለያዩ መድረኮች በሚኖራቸው ተሳትፎ በልማት  የበለፀጉ ሀገራት የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የጋራ  ዲፕሎማሲያው ጥረት ማድረግ አለብን ብለዋል።

ይህን መሰል ተግባራት በተቀናጀ መንገድ ለማስኬድ ዶሃ ፎረም ወሳኝ ሚና እንደሚወጣም ነው የገለጹት።

አምባሳደር ራባብ ፋጢማ በበኩላቸው ፥  ተመድ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ሀገራት፣ የባህር በር  የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት  እና ትናንሽ ደሴቶች ከድህነት ወጥተው ወደ ተሻለ የእድገት ሽግግር እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያም የዚህ ቡድን አባል ሀገር እንደ መሆኗ የበኩሏን ሚና እንድትጫወት አምባሳደሯ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.