በኦሮሚያ ክልል በ341 ሰዎች ላይ የሙስና ክስ ተመሰረተ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ341 ሰዎች ላይ የሙስና ክስ መመስረቱን በክልሉ የተቋቋመው የፀረ-ሙስና ኮሚቴ አስታውቋል።
በክልሉ የተቋቋመው እና ሰባት አባላት ያለው የፀረ-ሙስና ኮሚቴ እያከናወነ ያለውን ተግባር ተኮር ሥራ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው÷በኦሮሚያ ክልል ከሙስና ጋር በተያያዘ 16 መዝገቦች መከፈታቸውን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
በክልሉ የህብረተሰቡን ጥቆማ ተከትሎ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በ341 ሰዎች ላይ ክስ እንደተመሰረተባቸው በመግለጫው ተነስቷል፡፡
በተጨማሪም÷ በክልሉ ከሙስና ጋር በተያያዘ የተመዘበሩ የህዝብና መንግስት ንብረቶችን የማስመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ኮሚቴው ገልጿል፡፡
የሙስና ወንጀልን ለመከላከል እስካሁን ከኅብረተሰቡ በርካታ ጥቆማዎች እየመጡ መሆናቸው የተነሳ ሲሆን÷ ጥቆማው እውነታን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል፡፡
በክልሉ ኮሚቴው ከተቋቋመ ወዲህ 61 የሚሆኑ ጥቆማዎች ከኅብረተሰቡ መምጣታቸው ተመላክቷል።
በበኃይሉ ባኔ