የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዘመናዊ አዳዲስ ትጥቆች ባለቤት ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዘመናዊ አዳዲስ ትጥቆች ባለቤት መሆኑን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በስራ ላይ ያሰለጠናቸው የኮማንዶ እና የአድማ ብተና ኃይሎች በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያው የተግባር ልምምድ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም ኮማንዶ እና አድማ ብተና ኃይሎች የደረሱበት ብቃት እና የትጥቅ አቅሞች በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና በማኔጅመንት አባላት ተጎብኝቷል።
ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ” BRMD 2″ የተባለ ራሺያ ሰራሽ ባለ ጎማ ታንክ የትጥቅ ባለቤት መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተንቀሳቃሽና ቋሚ የደህንነት ካሜራዎችን ጭምር በመጠቀም ለአገርና ለህዝብ ሰላምና ደህንነት አስፈላጊውን ሁሉ ጥበቃ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።