Fana: At a Speed of Life!

የከተራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተራ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ።

ዛሬ በመላ ሀገሪቱ ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ ወርደዋል።

ታቦታት አዳራቸውን በጥምቀተ ባህር የሚያደርጉ ሲሆን፥ በካህናትና ዲያቆናት ዝማሬና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ይከወናሉ።

በነገው ዕለት ደግሞ የጥምቀት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የሚከበር ይሆናል።

የከተራና የጥምቀት በዓላት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በአደባባይ በድምቀት የሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.