የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራር ከሩሲያ ኩባንያዎች ቡድን መሪ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚና አመራሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው የማምረት ፍላጎት ካላቸው የሩሲያ ኩባንያዎች ቡድን መሪ ጋር ተወያይተዋል።
ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ሠባት ዓመታት ስላከናወናቸው እና ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ መሰረተ ልማቶች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎች ቀርበው ተወያይተውባቸዋል።
በቀጣይም ፍላጎት ያሳዩት ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በኢንዱስትሪ ፓርኮች አስፈላጊ የቅድመ ኢንቨስትመንት ምልከታዎችን የሚያደርጉበት ሁኔታ እንደሚኖር ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።