የሀገር ውስጥ ዜና

በደምበል ሐይቅ የከተራ በዓል በድምቀት ተከበረ

By Meseret Awoke

January 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለየት ያለው የደምበል ሐይቅ የጥምቀት ከተራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በደምበል ወይም በዝዋይ ሐይቅ አምስት ደሴቶች ያሉ ሲሆን ፥ በደሴቶቹ ከ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የታነጹ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ይገኛሉ።

በአካባቢው የከተራ በዓል ታቦታቱ ከየደሴቶቹ ወጥተው በአንድ ላይ በመሆን በማደሪያቸው ደርሰዋል ።

ምዕመኑ በታንኳ ላይ ሆነው ታቦታቱን ሲያጅቡ ልዩ ልዩ ትዕይንቶችን እያሳዩ በደምበል ሐይቅ ላይ መጓዛቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የከተራ በዓሉን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንና የባቱ ከተማ አስተዳደር በጋራ አስተባብረውታል።