Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በምጃር ሸንኮራ ወረዳ ኢራቡቲ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በምጃር ሸንኮራ ወረዳ በኢራቡቲ በድምቀት እየተከበረ ነው።
 
በዓሉ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁ ወቅዱስ አቡነ ቀለሚንጦስ በተገኙበት ነው በአምሳለ ዮርዳኖስ እየተከበረ የሚገኘው ።
 
44ቱ ታቦታት በትላንትናው ዕለት ከየአድባራቱ በካህናቱ፣ በዲያቆናቱ እንዲሁም በምዕመኑ ዝማሬ ታጅበው ወደአምሳለ ዮርዳኖስ ባህረ ጥምቀቱ ከደረሱ ብኋላ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎችን በመፈፀም ታድሯል ፡፡
 
ዛሬ ጠዋትም የቅዳሴ ስነ-ስርዓቱ ተከናውኖ በብፁ አቡነ ቀለሚንጦስ አምሳለ ዮርዳኖስ ተባርኮ ምዕመኑ ተጠምቋል።
 
በምጃር ሸንኮራ ኢራቡቲ የጥምቀት በዓል አከባበር ላይም ከአካባቢው ማህበረሰብ በተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ታድመዋል ።
 
በአበበ የሸዋልዑል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.