Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በሩሲያ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል በሀገረ ሩሲያ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአስቸጋሪ የክረምት ቅዝቃዜ በዓሉን እያከበሩ ያሉት ሩሲያውን በሐይማኖታዊ ባህላቸው መሰረት በቅዱስ መስቀል ቅርፅ በተሰራው እና ዮርዳኖስ ተብሎ በሚጠራው የበረዶ ጉድጓድ ውስጥ በመግባት ይጠመቃሉ፡፡

ይህ ስነ ስርዓት የሚከናወነውም ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ያደረገውን ጥምቀት ለማስታወስ መሆኑን ነው የተገለፀው፡፡

በዓሉን የሩሲው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ ሩሲውያን ዮርዳኖስ ተብሎ በሚጠራው የበረዶ ጉድጓድ በመጠመቅ እያከበሩት መሆኑን ከሩሲያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.