Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ትሩፋቱ በተጨማሪ የዓለም የቱሪዝም መስህብ ሆኗል – አቶ ቀጄላ መርዳሳ

በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ እሴቶችን ለመልካም እና በጎ ነገር ልንጠቀምባቸው ይገባል ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ፡፡
 
አቶ ቀጄላ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በተከበረው የጥምቀት በዓል በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
በመልዕክታቸውም ÷ኢየሱስ ክርስቶሰ በትህትና ራሱን ዝቅ አድረጎ በአገልጋዩ መጥምቁ ዮሃንሰ እጅ መጠመቁ የሰው ልጅ ራሱን የሚያድስበት፣ ራሱን የሚለውጥበት እና የሚያድንበትን መንገድ እንዲፈልግ እና መልካምነት እንዲላበሰ ምሳሌ ለመሆን ነው ብለዋል፡፡
 
ቀሳውስቱ ተሸክመው ወደ ባህረ ጥምቀቱ የሚወስዷቸው እና ወደ አድባራቱ የሚመልሷቸው ታቦታትም አትግደል፣ አትስረቅ ታላላቆችህን አክብር፣ሰዎችን እንደ ራስህ ውደድ የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን መያዛቸውን አንስተዋል፡፡
 
ስለሆነም በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ እሴቶችን እና አስተምህሮዎችን ለመልካም እና በጎ ነገር ልንጠቀምባቸው ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
ሃይማኖት ከፖለቲካ ነጻ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ÷ ሃይማኖትን ከፖለቲካ መቀላቀል እና ለፖለቲካ አላማ መጠቀም ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
 
የሃይማኖት በዓላት የሚከበሩባቸው ቦታዎች እና ስፍራዎች ሁሉ የተቀደሱ በመሆናቸው ሊከበሩ ይገባል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትሩፋቱ በተጨማሪ የቱሪዝም መስህብ በመሆን የሀገር ሃብት ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ መመዝገቡን አውስተዋል፡፡
 
ስለሆነም ባህላዊ እና መንፈሳዊ እሴቶቻችንን በጋራ ልንጠብቃቸው እና ልናሳድጋቸው ይገባል ሲሉ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡
 
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.