Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በሁለቱ ክልሎች ሠላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በአሶሳ ከተማ ተወያይተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ተገኝተዋል።

ውይይቱ በሁለቱ ክልሎች ተጎራባች አካባቢዎች ለሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ተጎራባች አካባቢዎች ሠላምን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ሥራዎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

ሠላምን በማረጋገጥ የተጀመሩ የሠላም፣ የጸጥታና የልማት ሥራዎችን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር አቅጣጫ መቀመጡንም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.