Fana: At a Speed of Life!

በጃንሜዳ በጥምቀት በዓል ላይ ስርቆት ፈጽመዋል የተባሉ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የከተራ እና ጥምቀት በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የተሰረቁ 20 ሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ስምንቱ ተጠርጣሪዎች በበዓሉ ዕለት ፀበል ለመረጨት የነበረውን ግፊያ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አምስቱ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር የዋሉት በከተራ በዓል ሲሆን÷ ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይም 3 ሞባይል ስልክ በኤግዚቢትነት ተይዟል ነው የተባለው፡፡

የሞባይል ስልክ የተሰረቀባቸው ጃንሜዳ በሚገኘው ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በማመልከታቸው የተወሰኑት ባለቤቶቻቸው መገኘታቸው እና ሌሎቹ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው መጠየቅ እንደሚችሉ ፖሊስ ገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.