ጥምቀትን በአብሮነት በማክበራችን ተደስተናል – የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓመታት ርቆን የቆየው ሰላም ተመልሶ ጥምቀትን በአብሮነት በማክበራችን ተደስተናል ሲሉ የአክሱም ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።
የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ አክሱም ከተማና ሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተከብሯል።
አስተያየት ሰጭዎቹ በመንግሥትና በህወሓት ታጣቂዎች የሰላም ስምምነት ከተፈጠረ በኋላ የሰላም ዓየር ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
የተጀመረውን ሰላም ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ ሁላችንም የሚጠበቅብንን እንወጣለን ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!