የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ ክልል የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

By Alemayehu Geremew

January 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ2015 የስድስት ወራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሔደ ነው፡፡

በግምገማው ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መሀመድ ሻሌን ጨምሮ የሁሉም መሥሪያ ቤቶች እና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ እንደገለጹት÷ የግምገማው ውጤትና ቀጣይ አቅጣጫ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል፡፡

የፋይናንስ አጠቃቀም፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የግብርና ሥራዎች፣ የሰላምና የፀጥታ እንዲሁም የአመራሩ አገልግሎት አሰጣጥ እና ተጠያቂነት በዋናነት በግምገማው ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

የፓርላማ፣ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት እና የክልሉ የክትትልና ቁጥጥር ቡድኖች በግምገማው እንደሚሳተፉ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡