Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዛሬ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡
 
ኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዘሃራ መሃመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ኢንተርፕራይዙ በታሪኩ የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ከባድ የትራፊክ አደጋ ባሳለፍነው ጥር 8 ቀን ማስተናገዱን አስታውሰዋል፡፡
 
ይህን ተከትሎም የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዝግ ተደርጎ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
 
አገልግሎቱን ወደ ቦታው ለመመለስና መንገዱን ለተጠቃሚዎች ክፍት ለማድረግ ከጽዳት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለሞያዎች ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡
 
በዛሬው ዕለት 3፡30 ጀምሮም የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.