በመዲናዋ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት የከተማ አውቶቡሶችን በተመለከተ÷ እስከ 4 ኪሎ ሜትር 1 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው እና ከ4 ነጥብ 1 እስከ 6 ኪሎ ሜትር 2 ብር የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 3 ብር፣ ከ6 ነጥብ 1 እስከ 8 ኪሎ ሜትር 2 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው እና ከ8 ነጥብ 1 እስከ 9 ኪሎ ሜትር 3 ብር የነበረው ታሪፍ በአዲሱ ማሻሻያ 5 ብር፣ ከ9 ነጥብ 1 እስከ 10 ኪሎ ሜትር 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው እና ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ኪሎ ሜትር 4 ብር የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 6 ብር እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል፡፡
ከ12 ነጥብ 1 እስከ 13 ኪሎ ሜትር 4 ብር ከ50 ሣንቲም፣ ከ13 ነጥብ 1 እስከ 15 ኪሎ ሜትር 5 ብር የነበረው እንዲሁም ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ኪሎ ሜትር 6 ብር የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 8 ብር ሆኗል፡፡
እንዲሁም ከ17 ነጥብ 1 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 7 ብር የነበረው 10 ብር እና ከ20 ነጥብ 1 ነጥብ እስከ 23 ኪሎ ሜትር 8 ብር የነበረው 10 ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ከ23 ነጥብ 1 እስከ 26 ኪሎ ሜትር 9 ብር የነበረው 15 ብር ፣ ከ26 ነጥብ 1 እስከ 30 ኪሎ ሜት 10 ብር የነበረው 15 ብር፣ ከ 30 ነጥብ 1 እስከ 35 ኪሎ ሜትር 12 ብር የነበረው 20 ብር፣ ከ35 ነጥብ 1 እስከ 40 ኪሎ ሜትር 15 ብር የነበረው 20 ብር፣ ከ40 ነጥብ 1 እስከ 45 ኪሎ ሜትር 15 ብር የነበረው 25 ብር፣ ከ45 ነጥብ 1 እስከ 50 ኪሎ ሜትር 20 ብር የነበረው 25 ብር እንዲሆን ተወስናል፡፡
የሃይገርና የቅጥቅጥ ታክሲዎች የታሪፍ ማሻሻያ በተመለከተ÷ እስከ 8 ኪሎ ሜትር 5 ብር የነበረው ታሪፍ በነበረው እንዲቀጥል፣ ከ8 ነጥብ 1 እስከ 12 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በአዲሱ ማሻሻያ 8 ብር፣ ከ12 ነጥብ 1 እስከ 16 ኪሎ ሜትር 9ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ ከነገ ጀምሮ በሚተገበረው ማሻሻያ 10 ብር እንዲሆን ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም ከ16 ነጥብ 1 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 12 ብር የነበረው ክፍያ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 13 ብር እንዲሁም ከ20 ነጥብ 1 እስከ 24 ኪሎ ሜትር 14 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 15 ብር፣ ከ24 ነጥብ 1 እስከ 28 ኪሎ ሜትር 17 ብር የነበረው 18 ብር እንዲሆን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ከ7 ነጥብ 6 እስከ 10 ኪሎ ሜትር 13 ብር የነበረው ታሪፍ በማሻሻው 14 ብር፣ ከ10 ነጥብ 1 እስከ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 16 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ 17 ብር፣ ከ12 ነጥብ 6 እስከ 15 ኪሎ ሜትር 19 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ 20 ብር ከ50 ሣንቲም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ከ15 ነጥብ 1 እስከ 17 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 23 ብር የነበረው 24 ብር፣ ከ17 ነጥብ 6 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 26 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በአዲሱ ማሻሻያ 27 ብር፣ ከ20 ነጥብ 1 እስከ 22 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 29 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በማሻሻያው 31 ብር ሆኗል፡፡
እንዲሁም ከ22 ነጥብ 6 እስከ 25ኪሎ ሜትር 33 ብር የነበረው ታሪፍ በማሻሻያው 34 ብር፣ ከ25 ነጥብ 1 እስከ 27 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 36 ብር የነበረው ታሪፍ 38 ብር፣ ከ27 ነጥብ 6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር 39 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ ማሻሻያ 41 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሚኒባስ ታክሲዎችን በተመለከተ÷ እስከ 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣ ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ሆኗል፡፡
በተጨማሪም ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5ኪሎ ሜትር 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን በተመለከተ÷ እስከ 17 ኪሎ ሜትር 4 ብር የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር እንዲሆን ቢሮው ውሳኔ አሳልፏል፡፡