Fana: At a Speed of Life!

የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለንዋይ የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ያዘጋጁት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያለመ ፎረም በህንድ ቼናይ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በፎረሙ በቼናይ ከተማ በፋርማሲዩቲካል፣ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ከ60 በላይ ባለሃብቶች እና አምራቾች ተሳትፈዋል፡፡
በኢንቨስትመንት ፎረሙ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ መሰረተ ልማቶችን፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችንና ጠቀሜታዎች ዙሪያ ገለጻ ተደርጓል፡፡
ባለ ሃብቶቹ በኢትዮጵያ በብዙ ዘርፍ ያልተነካ እና ግዙፍ የኢንቨስትመንት አቅም መኖሩን ገልጸው÷በፋርማሲዩቲካል፣ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ከፎረሙ ጎን ለጎንም በአጭር ጊዜ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ካሳዩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት መደረጉንም ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.