
አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ አትላንታ ጆርጂያ ቀጥታ በረራ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ አትላንታ ጆርጂያ ቀጥታ የመንገደኞች በረራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
የሚደረገው በረራም በሳምንት ለአራት ቀናት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካ ያለውን የበረራ መዳረሻ ቁጥር ከዋሺንግተን ዲሲ፣ ኒዋርክ፣ ኒው ዮርክ እና ቺካጎ በመቀጠል
አምስት እንደሚያደርሰው የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡