Fana: At a Speed of Life!

የኮንትሮባንድ እቃዎችን ለማሳለፍ የሞከሩ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው በሕገወጥ መንገድ የገቡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ለማሳለፍ የሞከሩ ሁለት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የኮቪድ-19 ስርጭትን ክትትል እና ቁጥጥር እንዲያደርጉ የተመደቡ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሠራተኞች ከውጭ ገቢ መንገደኞች የኮንትሮባንድ እቃን በመረከብ እና ደብቀው ለማሳለፍ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት  ጥር 12 እና 13  ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ሽፋን በማድረግ 42  ዘመናዊ የእጅ ስልኮች እና በርካታ የስማርት ስልክ ቦርድ ስክሪኖችን  በቦርሳ በመደበቅ ይዘው ለመውጣት የሞከሩ ሁለት  የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.