ስፓርት

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥር 20 ይጀመራል

By Melaku Gedif

January 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን ላለበት ውድድር ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ከፊታችን ጥር 20 ቀን ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በዚህ መሰረትም ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች የ12ኛ ሳምንቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም የ11ኛ ሳምንቱ ወላይታ ድቻ ከሲዳማ ቡና እሁድ ጥር 21 ቀን 2015 ዓ.ም 9፡00 ሰዓት ይካሄዳሉ፡፡

በተጨማሪም ከ14ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች ከጥር 23 እስከ መጋቢት 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከሐሙስ እስከ እሁድ ባሉ ቀናት በ9 እና 12 ሰዓት እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያፕሪሚየር ሊግ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!