Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪል ማህበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ÷ ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ጽንሰ ሀሳብ፣ የሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነትና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።

ሀገራዊ ምክክር ማካሄድ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም በማስፈን፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት መሆኑን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ሀገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት እንዲሳካ የሁሉም ተሳትፎና ድጋፍ አስፈላጊ በመሆኑ ኮሚሽኑ ከተለያዩ አካላት ጋር በተከታታይ እየተወያየ ነው ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.