የሀገር ውስጥ ዜና

በቀጣዮቹ 11 ቀናት በምዕራብና ምሥራቅ ኢትዮጵያ ክፍል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል-ኢንስቲትዩቱ

By Meseret Awoke

January 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት 11 ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በተወሰኑ የሰሜን ምሥራቅ እና የምሥራቅ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎች አመላከቱ፡፡

በቀጣዮቹ 11 ቀናት በመደበኛ ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ ክፍሎች የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

በደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ እንደሚሄድም የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል በሚቀጥሉት 11 ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በጥቂት የሰሜን ምሥራቅ እና የምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎች ማመላከታቸውን የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ መረጃ ያሳያል፡፡

እንዲሁም የሰሜን፣ የሰሜን ምዕራብ፣ የደቡብ ምሥራቅና የመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የበጋው ደረቅ፤ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖ ይቆያል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!