የሀገር ውስጥ ዜና

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

January 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 173 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ከሕዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 31 ሺህ 919 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡