Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2015 የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2015 ዓ.ም ክልላዊ የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ስራ በይፋ ተጀምሯል።

የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ መንደር 52 ቀበሌ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በክልሉ ለሁለት ወራት በሚቆየው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ አመራሩ፣ ባለሙያው፣ አርሶ አደሩና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሣተፉ አቶ ባበክር ኻሊፋ ጥሪ አቅርበዋል።

በዘንድሮ የበጋ ወቅት ከ54 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ለማልማት መታቀዱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.