የሀገር ውስጥ ዜና

ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች

By Feven Bishaw

January 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዴንማርክ የልማት ትብብር እና ዓለምአቀፍ አየር ንብረት ሚኒስትር ዳን ጃርገንስ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይቱም አቶ ደመቀ÷ ዴንማርክ የኢትዮጵያ ቁልፍ የልማት አጋር መሆኗን አስታውሰው ሁለቱ ሃገራት በተለያዩ የትብብር መስኮች ግንኙታቸው እንዲጠናከር የኢትዮጵያ ፍላጎት መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በሰላም ስምምምነቱ አተገባበር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን÷መንግስት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።