የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባዎች በአፍሪካ የከንቲባዎች ፎረም ላይ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ

By Mikias Ayele

January 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ፣ ባሕርዳር፣ አዳማ እና ደሴ ከተማ ከንቲባዎች በደቡብ አፍሪካ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ የከንቲባዎች ፎረም ላይ የልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪኑሚ አዲንስያ በመድረኩ  ባደረጉት ንግግር÷ የአፍሪካ ልማት ባንክ ከተሞችን ለነዋሪቻቸው ምቹ ለማድረግ የሚያስችል ብድር (ፈንድ) ማቅረብ ይጀመራል ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ከተሞችና ከንቲባዎች  ከሕዝብ ፍላጎት በመነጨ ነገን ታሳቢ ያደረጉ ረጅምና ትውልድ የሚሻገሩ ዘላቂ ዐሻራን እያሳረፉ መሄድ እንደሚገባ ከንቲባዎቹ ተናግረዋል፡፡

በልምድ ልውውጡ የተካፈሉ ከንቲባዎች÷ ከተሞችን  ለነዋሪዎች  ምቹ  በማድረግ  ማገልገል በትኩረት ሊሠራበት ይገባል ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በልምድ ልውውጡ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡