Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ ዓመቱ ከ225 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሥድስት ወራት ከ225 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ባለፉት ስድስት ወራት በገቢ አሰባሰብ ላይ የተሰሩ ስራዎችን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም÷ ለመሰብሰብ ከታቀደው 228 ቢሊየን 229 ሚሊየን 60 ሺህ 140 ብር ውስጥ 225 ቢሊየን 933 ሚሊየን 8 ሺህ 25 ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 99 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ54 ቢሊየን 622 ሚሊየን 624 ሺህ 687 ብር ብልጫ እንዳለውም ነው የተናገሩት።

ገቢው ከሀገር ውስጥ ታክስ፣ ከወጪ ንግድና ቀረጥ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች እንደተሰበሰበ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀሪ ሥድስት ወራትም የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ግብር ከፋዮችም ሆኑ የተቋሙ ሰራተኞች ተቀራርበው በመስራት ለግብር አሰባሰቡ ውጤታማ መሆን ሊረባረቡ እና ሊተጉ እንደሚገባ  ሚኒስትሯ አስገንዝበዋል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.