Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተመድ ያላትን የሠላም ማሥከበር ተሳትፎ አጠናክራ ትቀጥላለች – ሜ/ጄ አዳምነህ መንግስቴ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያላትን የሰላም ማስከበር ተሳትፎ አሁን ባለው አግባብ ማስቀጠል እንድትችል ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ፡፡

አዛዡ በማዕከሉ በተካሄደው የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ውይይት ፥ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን ተሳትፎ ለማሥቀጠል የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማሣደግና ድክመቶችን ማረም ይገባል ብለዋል፡፡

በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የመንግስት ንብረቶችን በመጠገንና ወደ ስራ በመመለስ የተከናወኑ ወጪ ቆጣቢ አሰራሮች በሌሎችም ክፍሎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም አርአያነታቸውን አድንቀዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ጋር የነበሩ ውጤታማ ስራዎችና ስልጠናዎች፣ ለዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሰራዊትን በብቃት የማዘጋጀትና የግንባታ ስራዎች እንዲሁም የሎጅስቲክስ ዝግጅት ስምሪትና ድጋፎች፣ የዘመቻ ስምሪትና ሚሽን ክትትል፣ አስተዳደራዊና የፋይናንስ ስራዎች፣ የስራ አፈፃፀም ሂደት በጥንካሬ ተገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የተሰማራው የሰላም አስከባሪ ሃይል የሚያከናውናቸውን ውጤታማ የሰላም ማስከበር ስራዎች በማስቀጠልና የኢትዮጵያን ተሠሚነት በተሻለ ደረጃ ማሣደግ እንደሚገባ አዛዡ ገልፀዋል፡፡

ክፍተቶችን ለመሙላት በስልጠና አቅምን በየሙያ ዘርፉ በማሳደግ የአቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚኖርባቸው ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.