የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ከ3 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዘገቡ

By Alemayehu Geremew

January 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ 3 ሚሊየን 28 ሺህ 770 መራጮች ተመዘገቡ፡፡

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች ማለትም ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ እና ጎፋ እንዲሁም በአምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም በቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ እና ደራሼ ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ በ3 ሺህ 769 ምርጫ ጣቢያዎች ባካሄደው የመራጮች ምዝገባ በአጠቃላይ 3 ሚሊየን 28 ሺህ 770 መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ከተመዝጋቢዎች ውስጥ 493 የአካል ጉዳተኞች እንደሚገኙበትም ጠቁሟል፡፡

የተመዝጋቢው ቁጥር በፆታ ሲገለጽም 1 ሚሊየን 575 ሺህ 371 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 1 ሚሊየን 453 ሺህ 399ኙ ሴቶች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡