Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን የጦር ታንክ ድጋፏን በአውሮፓ በኩል ወደ ዩክሬን ልትልክ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ጀርመን የጦር ታንኮቿን በድጋፍ ወደ ዩክሬንለመላክ ጥርጊያ መንገዱን እያመቻቸች መሆኑ ተገለጸ፡፡

በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ ጀርመን 14 “ሊዮፓርድ ሁለት” የተሰኙ ታንኮቿን በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የትራንስፖርት ድጋፍ ወደ ዩክሬን እንደምትልክ ገልጻለች፡፡

ከዚህ ባለፈም ሌሎች ሀገራት ጀርመን ሰራሽ የሆኑ ታንኮችን ለዩክሬን ድጋፍ እንዲያደርጉ ይሁንታን ሰጥታለች።

ዩክሬን ድጋፉ በጦርነቱ ዐውድ ለውጥ የማምጣት ዐቅም አለው በማለት እያሞካሸችው ነው፡፡

ሁኔታውን በአፅንዖት እየተመለከተች ያለችው ሩሲያ በቀጣናው እየተባባሰ ከመጣው ውጥረት ጋር ተዳምሮ ድርጊቱን ኮንናዋለች፡፡

ሞስኮ መሰል ድርጊቶች ውጥረቱን በማባባስ ጦርነቱን ያራዝመዋል ስትል አስጠንቅቃለች።

ዩክሬን ምዕራባውያኑ በአስቸጋሪ የጦር አውድማ ላይ የተሻለ የመተኮስ ፣ ራሳቸውን የመከላከል ፣ በአስቸጋሪ መልክዓ-ምድሮች ያለ ችግር ተንቀሳቅሶ ጠላትን የማጥቃት ብቃት ያላቸውን የውጊያ ታንኮች እንዲሰጧት ለወራት ስትወተውት ቆይታለች፡፡

እንደ ዩክሬን ሐሳብ ቢሆን ሩሲያን በታንኮቹ አጥቅታ የተነጠቀቻቸውን መሬቶች መልሳ መያዝ ትፈልጋለች፡፡

የጀርመኑ ቻንስለር ዖላፍ ሾልዝ ÷ ዩክሬንን በተመለከተ ጀርመን ድጋፍ ለመሥጠት አታመነታም ፤ እንዲያውም በግንባር ቀደምትነት ትሠለፋለች ሲሉ በሀገራቸው ፓርላማ ባደረጉት ንግግር አድናቆትና ጭብጨባ ተችሯቸዋል፡፡

ንግግራቸውን ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በግል ሥልክ ደውለው ማመስገናቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ጀርመን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ባደርግም ጎራ ለይቸ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ አልገባሁም ብላለች፡፡

አሜሪካም ጀርመንን ተከትላ ለዩክሬን ተመሳሳይ የጦር ድጋፍ እንደምትልክ ቃል ገብታለች፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.