የሀገር ውስጥ ዜና

አይ ሲ ቲ ፓርክን በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ለማስገባት ያለመ ውይይት ተካሄደ

By Alemayehu Geremew

January 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አይ ሲ ቲ ፓርክን በሙሉ አቅሙና በአዲስ መልክ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ፡፡

ውይይቱን ያዘጋጀው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎትና ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ የአይ ሲ ቲ ፓርኩን ወደ ሥራ ለማስገባት ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን በቅንጅት ለማሟላት መክረዋል፡፡

በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና የተቋም ደኅንነት ጥበቃ ለማስጀመር ከሁለቱ ተቋማት ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አገልግሎቱን ለማሳለጥ ከሚመለከታቸው ሌሎች ተቋማት ጋር ተከታታይ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡