Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የሚመክር ቡድን ዛሬ ወደ መቀሌ ያቀናል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት አባላት ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ዛሬ ወደ መቀሌ ያቀናል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ቡድኑ ወደ መቀሌ የሚያቀናው በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ለመምከር ነው፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ ቡድን በመቀሌ ቆይታው ከመቀሌ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር ትምህርት ዳግም መጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም በትግራይ ክልል አጠቃላይ ትምህርትን ዳግም ለማስጀመር በሚቻልበባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቅንቶ በዩኒቨርሲቲው ዳግም የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.