ለጤናው ዘርፍ ውጤታማነት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ያስፈልጋል- ዶ/ር ሊያ ታደሰ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ለጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ቢሆንም ዘርፉን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ግን የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡
የ “ኢንቨስንት ኦርጅንስ 2023” የኢንቨስትመንት ዓለም አቀፍ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በፎረሙ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ በሦስተኛና በአራተኛ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘርፍ ያልተነካ የኢንቨስትመንት ዕድል አለ ብለዋል፡፡
በዘርፉ የሚሳተፉትን ለማበረታታትም የፖሊሲ ማሻሻያና ሌሎች ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በክትባት፣ በሕክምና ቁሳቁስ አቅርቦትና የጤና መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ሰፊ ዕድሎች እንዳሉ ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡
በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮችን ከማስተዋወቅ ባለፈ የልምድ ልውውጥ ይደረግታል ነው የተባለው፡፡
ባለሃቶች፣ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በፎረሙ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ እና አዳነች አበበ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!