Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የተገነባው ሀይሌ ግራንድ ሆቴል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ በአዲስ አበባ ከተማ ያስገነባው ሀይሌ ግራንድ ሆቴል ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የሆቴሉን ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ሆቴሉ በዚህ ወቅት ፥ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እንደተሰራ ገልጾ ውድድራችን ከዓለም አቀፍ የሆቴል ኢንዱስትሪው ጋር ነው ብሏል።

በሆቴል እና ሪዞርት መስክ በ12 ዓመት ውስጥ ስምንተኛ የሆነው ይህ ሆቴል ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በመሆን ነው ስራውን የጀመረው፡፡

ልዩነትን እና የላቀ አገልግሎት መስጠትን መሰረት አድርገን እየሰራን ነው ያለው አትሌት ኃይሌ ፥ በቀጣይም ከሀገር ውጭ ባሉ ከተሞች በማስፋት የመስራት እቅድ እንዳለም አንስቷል፡፡

በትዕግስት አስማማው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.