የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

By Amele Demsew

January 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ የሚውል 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ በዚህ ወቅት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በኮቪድ-19፣ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በደረሰ አደጋና የነበረውን ግጭት ጨምሮ ብዙ ቀውሶች መድረሱን አመላክቷል።

የጤና አገልግሎቶችን አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ በመስተጓጎሉም ባለፉት አስርት ዓመታት በሀገሪቷ የተመዘገበው የጤና ውጤት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቧልም ነው ያለው፡፡

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ወደ 24 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በቂ የጤና አገልግሎት እያገኙ ባለመሆኑ ድጋፉ ለዚህ አገልግሎት እንደሚውል ተገልጿል።

በቅድስት ተስፋዬ