የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሦስትዮሽ መፍትሔ አፈላላጊ ቡድን አባላት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

January 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ቆይታቸው በፖለቲካው ሂደት ላይ ከተሰማሩ የተለያዩ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሦስትዮሽ መፍትሔ አፈላላጊ ቡድን አባላት ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብ ያልሆነ መርሕ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር የሚሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የሱዳን ሕዝብ እና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን እንዲፈልጉም ማበረታታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሥራ ጉብኝት ወደ ሱዳን ካርቱም ማቅናታቸው ይታወቃል፡፡