Fana: At a Speed of Life!

ለ44ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ የካቲት 18 ቀን 2023 በአውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ለሚካሄደው 44ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ 14 ወንድና 14 ሴት አትሌቶች ከነተጠባባቂዎቹ ከ40ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በወጣትና በአዋቂ ምድብ መመልመላቸው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም አትሌቶቹ ከውድድሩ ማግስት ጀምሮ በማሰልጠኛ ማዕከል ሆነው ልምምዳቸውን እያካሄዱ መሆኑን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም መሰረት፡- በወጣት ሴቶች 6 ኪሜ( 6 አትሌቶች)፣ በአዋቂ ሴቶች 10 ኪሜ( 6 አትሌቶች)፣ በወጣት ወንዶች 8 ኪሜ (6 አትሌቶች) እና በአዋቂ ወንዶች 10 ኪሜ (6 አትሌቶች) ተመልምለው ልምም እያደረጉ ነው፡፡

በድብልቅ ሪሌይ 2 ወንድና 2 ሴት አትሌቶች በድምሩ 28 አትሌቶች ተመልምለው ከ8 አሰልጣኞች ጋር በስልጠና ማዕከል ስልጠናና የጤና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.