Fana: At a Speed of Life!

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 160 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መለሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባበር 160 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መልሷል፡፡

ፍልሰተኞቹ የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀትና ግንዛቤ በማስጨበጥ ነው ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው።

ከተመላሾቹ መካከል 32ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ሲሆን፥ 23 ያህሉ ሴቶች እና በጉዞ ወቅት የወለዱና ነፍሰ ጡርም ይገኙበታል፡፡

116ቱ ፍልሰተኞች የመን ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው ወደ ጅቡቲ የገቡ ሲሆኑ ፥ ጂቡቲ ደርሰው የተመለሱት 44 ፍልሰተኞችም በመሸጋገሪያና መዳረሻ ሀገራት ለከፍተኛ እንግልትና ተያያዥ ችግሮች መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ-ጅቡቲ-የመን የሚደረገው ህገወጥ የሰዎች ፍልሰት በአደጋዎች የተሞላ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ ከጅቡቲ በመነሳት ቀይ ባህርን በማቋረጥ ላይ እያሉ 6 የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ጀልባዎች ላይ በደረሱ አደጋዎች ከ118 በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.