Fana: At a Speed of Life!

ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ትራንስፖርት ለማስጀመር ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ትራንስፖርት ለማስጀመር ለማኅበራት መመሪያ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ በሰላም ሚኒስትሩ የሚመራው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እንደፈቀደ አገልግሎቱ ይጀመራል፡፡

በዚሁ መሰረት የአገር አቋራጭ፣ ልዩ አውቶቡስ፣ መደበኛ አውቶብስ እና ሌሎችም የትራንስፖርት ሰጪ ማኅበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል፡፡

አገልግሎቱም ቀደም ሲል በነበረው መስመር መሰረት መቀሌ፣ አክሱም እና ሽረን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች ይጀመራል ነው የተባለው።

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.