የሀገር ውስጥ ዜና

2 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ከውጭ በቅርቡ ይገባል

By ዮሐንስ ደርበው

January 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2 ሚሊየን ኩንታር ስኳር በቅርቡ ከውጭ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡

ለግዥውም 110 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ስኳሩም ከብራዚል መገዛቱን ነው በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሕዝብ ግንኙነትና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ረታ ደመቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለፁት።

የስኳር ምርቱ በአራት ዙር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡

ከግዥ ጋር በተያያዘ በተቋሙ በኩል ያሉ ስራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!