Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ “ኤም ዋን አብራምስ” እና “ሊዮፓርድ 2” ታንኮችን የሚያወድም ሮቦት ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ “ኤም ዋን አብራምስ” እና “ሊዮፓርድ 2” የተባሉ ታንኮችን የሚያወድም አዲስ ሮቦት ያፋ ማድረጓን ይፋ አድርጋለች፡፡

ባለፈው ረቡዕ በርሊን እና ዋሺንግተን “ኤም ዋን አብራምስ” እና “ሊዮፓርድ 2” ታንኮችን ለዩክሬን ለመላክ ዝግጁ እንደሆኑ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትሎም ሩሲያ የጠላትን ታንክ በመለየት የሚያወድም ዘመናዊ ሮቦት መስራቷ ተሰምቷል።

ይህ አዲሱ ሩሲያ ሰራሽ ሮቦት የጀርመን እና የአሜሪካ ስሪት የሆኑ የጦር ታንኮችን ማውደም የሚችል መሆኑን የቀድሞ የሩሲያ የጠፈር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዲሚትሪ ሮጎዚን ለስፑትኒክ ተናግረዋል ።

ሮቦቱ የጠላትን ወገን ዒላማዎች እና እንቅስቃሴን በምስል አስደግፎ የሚያሳይ መሳሪያ ተገጥሞለታል።

በዋናነትም የታንኮቹን እንቅስቃሴ ከተመለከተ በኋላ በሚሳኤል ማውደም ይችላልም ነው የተባለው።

በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይም አራት ሮቦቶች በዶንባስ ክልል ሙከራ ካደረጉ በኋላ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.