Fana: At a Speed of Life!

በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ጊዜያዊ ማገገሚያ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የተሃድሶ ማዕከል እድሳት ተደርጎለት ከፍተኛ የመንግስት አካላት በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ-ስረዓቱ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡመድ ÷በማዕከሉ ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት ልዩ ልዩ ድጋፎችን የሚያገኙበት ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በቀጣይ ከማህበረሠቡጋር በመቀላቀል መደበኛ ህይወት እንዲመሩ የሚያስችሉ ስራዎች የሚከናወኑበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሀገር ላይ የተፈጠረውን አደጋ ለመቅረፍ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ግለሰቦችና ባለሃብቶች በጋራ በመስራት መፍትሄ ማምጣት ተገቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ በተደረገው የምክክር መድረክ በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች የደረሱ አጠቃላይ ጉዳቶችን በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት መቅረቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጥናቱም ግጭት በደረሰባቸው አከባቢዎች የደረሱ ጉዳቶችን በተለይም ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች በመደገፍ የተሰሩ ስራዎች፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስፈልጉ ድጋፎች ተመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.