Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 173 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 173 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ፡፡

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት ዜጎች መካከል 1 ሺህ 135ቱ ወንዶች፣ 5ቱ ሴቶች እና 33ቱ ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 35 ሺህ 249 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.