Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ባለፉት ሥድሥት ወራት 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ባለፉት ሥድሥት ወራት 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

የሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሥድሥት ወራት ከእቅድ በላይ ገቢ ለሰበሰቡ የከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች የማበረታቻ የእውቅና ሽልማት አበርክቷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ዑስማን በክልሉ በ2015 በጀት አመት ለመሰብሰብ ታቅዶ ከነበረው 9 ቢሊየን ብር ገቢ በግማሽ አመቱ የእቅዱን ግማሽ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

በክልሉ የገቢ አስባሰብ ስርአቱን ለማሻሻል  የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

ባለፉት 4 አመታት ተኩል ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገለፁት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ይህ ገቢ በክልሉ የገቢ አሰባበሰብ ታሪክ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲአዚዝ አህመድ በበኩላቸው ቢሮው በመጀመሪያው ሥድሥት ወር ለመሰብሰብ ያቀደውን ገቢ ሙሉ በሙሉ ማሳካቱን አንስተዋል፡፡

ይህን ውጤት በማጠናከር በቀጣይ የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለመሰብሰብ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ማለታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.